የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት በዕቅድ የተያዙ የጥገና መስመሮች ሙሉ በሙሉ በመጠገን መንገዶቹ ለህብረተሰቡ ተገቢዉን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እየሰራ ነዉ፡፡
በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ ነባር የገጠር መንገዶች ተገቢዉን ጥገና እንዲያገኙ በማድረግ ህብረተሰቡ ያልተቋረጠ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ እየሰራ ያለ ጥገና ጽ/ቤት ነዉ፡፡
ጥገና ጽ/ቤቱ በተያዘዉ በጀት ዓመት በ38 የጥገና መስመሮች በመደበኛ እና ወቅታዊ የጥገና ዓይነቶች 953 ኪ.ሜ የነባር ገጠር መንገዶች ጥገና ለማከናወን አቅዶ እስከ ታህሳሥ 15/2018 ዓ.ም ባለዉ ጊዜ በ23 የጥገና መስመሮች 519.18 ኪ.ሜ መንገድ በመጠገን እስከ ታህሳስ አጋማሽ የተያዘዉን ዕቅድ 129.8%፣የዓመቱን ዕቅድ ደግሞ 54.5% መፈፀም ችሏል፡፡ከተከናወነዉ የጥገና ሥራ መካከል 464.27 ኪ.ሜ(89.4%) የሚሆነዉ መደበኛ ጥገና ሲሆን ቀሪዉ 54.91 ኪ.ሜ(10.6%) የሚሆነዉ ደግሞ ወቅታዊ ጥገና ነዉ፡፡
ጥገና ጽ/ቤቱ በአሁኑ ወቅት 103.2 ኪ.ሜ ርዝመት ባላቸዉ ከደጋን -አዳሜ፣በለጩማ-ዴንሳ፣ወይናምባ-ልጓማ እና ከመሳለሚያ-ሾላዉ 4/አራት/ የጥገና መስመሮች በመደበኛ እና ወቅታዊ የጥገና ዓይነቶች የጥገና ሥራ እያከናወነ ሲሆን የጥገና ሥራዉን በጥር ወር ዉስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነዉ፡፡
የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ በዕቅድ የተያዙ ሁሉም የጥገና መስመሮች የጥገና ሽፋን እንዲያገኙ በማድረግ የዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡




