የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ሰራተኞች በኤች. አይ. ቪ/ኤድስ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄዱ።

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ሰራተኞች ከክልሉ ጤና ቢሮ በመጡ ባለሙያዎች በያመቱ ህዳር 22 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የኤች. አይ. ቪ/ኤድስ ቀን ምክንያት በማድረግ ዓለም አቀፋዊ ፣ አገራዊና ክልላዊ የኤች. አይ. ቪ/ኤድስ ነባራዊ ሁኔታን መሰረት ያደረገ ፅሁፍ ቀርቦ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ህዳር 27/2018 ዓ.ም አካሂደዋል።

የ2018 ዓ.ም የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ38ኛ ጊዜ ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ37ኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን የዘንድሮው የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቀን በአገራችን "ተግዳሮቶችን በመቋቋም የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምላሽን እናረጋግጣለን!" በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል።

ለኤጀንሲው ሰራተኞች በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዙሪያ ከተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ በተጨማሪ የአካል ጉዳተኞችንና ህፃናትን አስመልክቶ ከክልሉ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በመጡ ባለሙያዎች ለውይይት መነሻ የሚሆን ፅሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በውይይቱም አካል ጉዳተኞችና ህፃናት እንክብካቤና ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በመሆናቸው ሁሉም አካል ከማንኛውም ጉዳት ሊጠብቃቸው እንደሚገባ ግንዛቤ ተፈጥሯል ።