የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን በላቀ ደረጃ ለመፈፀም ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት፣ በመተጋገዝ እና በመናበብ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ፡፡


የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክስን ኤጀንሲ በ2017 ዓ.ም የተሻለ ለፈፀሙ እውቅና የመስጠት እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መስከረም 12/2018 ዓ.ም በተካሄደበት ወቅት በመድረኩ የተገኙት የአብክመ መንገድ ቢሮ ኃላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ/ር) ባስተላለፋት መልዕክት ክልሉ ከ2018 በጀት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የ25 ዓመት አሻጋሪ እና የ5 ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ስራ የተገባ መሆኑን ጠቅሰው ኤጀንሲው በአሻጋሪ እና በ5 ዓመቱ ስትራቴጅክ ዕቅድ የተቀመጡ የመንገድ ልማት ግቦች እንዲሳኩ የበኩሉን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት በትጋትና በቁጭት መስራት የሚጠበቅበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ኤጀንሲው በ2017 ዓ.ም በክልሉ የተሻለ አፈፃፀም ካስመዘገቡ ተቋማት መካከል አንዱ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ጋሻው የ2018 ዓ.ም የመንገድ ልማት ዕቅድ በላቀ ደረጃ ለመፈፀም ከሚመለከታቸዉ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት፣ በመተጋገዝ እና በመናበብ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ከዞን እና ወረዳ አስተዳደር አካላት እንዲሁም ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ለመፈፀም የሚያግዝ አስቻይ ሁኔታ እንዲፈጠር በትኩረት መሰራት እንዳለበትም አክለው ገልፀዋል፡፡
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቀለሙ ሙሉነህ በበኩላቸዉ ኤጀንሲው ባለፈው በጀት ዓመት በፈተና ውስጥ ሆኖ ፈተናዎችን በብልሃት እና በትዕግስት በማለፍ እንዲሁም የህይወት መስዋትነትም ጭምር በመክፈል ውጤታማ አፈፃፀም ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ለመፈፀም እንዲቻል በቅርቡ ወደ ስራ ለመግባት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ዕቅዱን በተነሳሽነት እና በባለቤትነት ስሜት በመስራት በወቅቱ ለማሳካት እንዲቻል በክላስተር ደረጃ ተመሳሳይ የዕቅድ ትውውቅ መድረኮች በማዘጋጀት በዕቅዱ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሚሰራም ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት በ34 የመንገድ እና ድልድይ ኘሮጀክቶች 102.15 ኪ.ሜ መንገድ እና 227 የተለያዩ መጠን ያላቸዉ ስትራክቸሮች ግንባታ ለማከናወን እንዲሁም በመደበኛ እና በወቅታዊ የጥገና አይነቶች በድምሩ 6,038 ኪ.ሜ የነባር ገጠር መንገዶች ጥገና ለማከናወን አቅዶ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
በዕውቅና እና በዕቅድ ትዉውቅ መድረኩ በ2017 ዓ.ም የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የዋናው መ/ቤት የሥራ ሂደቶች፣ የገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤቶች እና የመንገድ ሥራ ኘሮጀክቶች ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡ ከዋናው መ/ቤት የህግ አገልግሎት ክፍል ፣ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ፣ የዕቅድ ዝግጅት ፣ክትትል ና ግምገማ ደጋፊ የሥራ ሂደት፣ ከስድስቱ የገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤቶች የጐጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት፣ የወልዲያ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት እና የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት፣ ከ38 የመንገድ እና ድልድይ ኘሮጀክቶች የአምባጊዮርጊስ-ስላሬ፣ የጭምት- ማይ አንገታም ሎት-1 እና የባቲ-ጋራሮ-ኤላ የመንገድ ስራ ኘሮጀክቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመውጣት የዕውቅና የምስክር ወረቀት እና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ለገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤቶችና ኘሮጀክቶች ከተሰጠው የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ሽልማት በተጨማሪ ለጥገና ጽ/ቤትና ኘሮጀክት ማኔጅመንት አባላት ጥገና ጽ/ቤቶችና ኘሮጀክቶች ባስመዘገቡት የአፈፃፀም ደረጃ ቅደም ተከተል መሰረት የብር 1,000.00 /አንድ ሽህ ብር /፣ የብር 500.00 /አምስት መቶ/ እና የብር 250.00/ሁለት መቶ ሃምሳ / የሞባይል ካርድ የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በዕውቅና እና ዕቅድ ትውውቅ መድረኩ የኤጀንሲው ዋና መ/ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች፣ የገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት እና የኘሮጀክት ኃላፊዎች፣ የአብክመ መንገድ ቢሮ አመራሮች እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጥሪ የተደረገላቸዉ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

 

 

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ አመራሮች እና ሰራተኞች በቅርቡ ተጠናቆ በተመረቀዉ

የህዳሴ ግድብ ዙሪያ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር ያለመ ዉይይት አካሄዱ፡፡

የኤጀንሲዉ አመራሮች እና ሰራተኞች ‹‹እምርታ እና ማንሰራራት!›› በሚል መሪ ሀሳብ መጋቢት 24/2003 ዓ.ም ተጀምሮ ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም የተመረቀዉን የህዳሴ ግድብ አስመልክቶ የተዘጋጀዉን ሰነድ መሰረት በማድረግ በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ዉይይት በ5/01/2018 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡ የህዳሴ ግድብ ያለ ምንም የዉጭ የፋይናንስ ድጋፍ በኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት አቅም የተገነባ የኢትዮጵያዊያን የነፃነት እና የመቻል ምልክት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በዉይይቱ ግድቡ ሲገነባ ገጥመዉት በነበሩ ፈተናዎች፣በግድቡ ፋይዳ፣የህዳሴ ግድብን በመገንባት ሂደት በተወሰደ ትምህርት እና መሰል ጉዳዮች የጋራ ግንዛቤ እንዲፈጠር ተደርጓል፡፡

 

   

 

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ እና የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ አስመልክቶ በክልል ደረጃ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ተሳትፈዋል።

 በድጋፍ ሰልፉም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዳግም አድዋ ድል እና የህልውናችን መሰረት ስለመሆኑ፥ ስንተባበር የምንችል መሆኑን የሚገልፁና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ሰራተኞች በከፍተኛ ስሜት የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊ ሆነዋል።

           

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ አመራሮች እና ሰራተኞች በቅርቡ ተጠናቆ በተመረቀዉ

የህዳሴ ግድብ ዙሪያ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር ያለመ ዉይይት አካሄዱ፡፡

የኤጀንሲዉ አመራሮች እና ሰራተኞች ‹‹እምርታ እና ማንሰራራት!›› በሚል መሪ ሀሳብ መጋቢት 24/2003 ዓ.ም ተጀምሮ ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም የተመረቀዉን የህዳሴ ግድብ አስመልክቶ የተዘጋጀዉን ሰነድ መሰረት በማድረግ በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ዉይይት በ5/01/2018 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡ የህዳሴ ግድብ ያለ ምንም የዉጭ የፋይናንስ ድጋፍ በኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት አቅም የተገነባ የኢትዮጵያዊያን የነፃነት እና የመቻል ምልክት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በዉይይቱ ግድቡ ሲገነባ ገጥመዉት በነበሩ ፈተናዎች፣በግድቡ ፋይዳ፣የህዳሴ ግድብን በመገንባት ሂደት በተወሰደ ትምህርት እና መሰል ጉዳዮች የጋራ ግንዛቤ እንዲፈጠር ተደርጓል፡፡