የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት በዕቅድ የተያዙ የጥገና መስመሮች ሙሉ በሙሉ በመጠገን መንገዶቹ ለህብረተሰቡ ተገቢዉን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እየሰራ ነዉ፡፡
በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ ነባር የገጠር መንገዶች ተገቢዉን ጥገና እንዲያገኙ በማድረግ ህብረተሰቡ ያልተቋረጠ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ እየሰራ ያለ ጥገና ጽ/ቤት ነዉ፡፡
ጥገና ጽ/ቤቱ በተያዘዉ በጀት ዓመት በ38 የጥገና መስመሮች በመደበኛ እና ወቅታዊ የጥገና ዓይነቶች 953 ኪ.ሜ የነባር ገጠር መንገዶች ጥገና ለማከናወን አቅዶ እስከ ታህሳሥ 15/2018 ዓ.ም ባለዉ ጊዜ በ23 የጥገና መስመሮች 519.18 ኪ.ሜ መንገድ በመጠገን እስከ ታህሳስ አጋማሽ የተያዘዉን ዕቅድ 129.8%፣የዓመቱን ዕቅድ ደግሞ 54.5% መፈፀም ችሏል፡፡ከተከናወነዉ የጥገና ሥራ መካከል 464.27 ኪ.ሜ(89.4%) የሚሆነዉ መደበኛ ጥገና ሲሆን ቀሪዉ 54.91 ኪ.ሜ(10.6%) የሚሆነዉ ደግሞ ወቅታዊ ጥገና ነዉ፡፡
ጥገና ጽ/ቤቱ በአሁኑ ወቅት 103.2 ኪ.ሜ ርዝመት ባላቸዉ ከደጋን -አዳሜ፣በለጩማ-ዴንሳ፣ወይናምባ-ልጓማ እና ከመሳለሚያ-ሾላዉ 4/አራት/ የጥገና መስመሮች በመደበኛ እና ወቅታዊ የጥገና ዓይነቶች የጥገና ሥራ እያከናወነ ሲሆን የጥገና ሥራዉን በጥር ወር ዉስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነዉ፡፡
የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ በዕቅድ የተያዙ ሁሉም የጥገና መስመሮች የጥገና ሽፋን እንዲያገኙ በማድረግ የዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡




የጎጃም
የጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ባለፉት 5 ወራት ከ300 ኪሜ በላይ የነባር ገጠር መንገዶች ጥገና ሥራ አከናወነ፡፡
በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት እስከ ህዳር መጨረሻ 2018 ዓ.ም ድረስ 295.21 ኪሜ የነባር ገጠር መንገዶች ጥገና ለማከናወን አቅዶ በመደበኛ እና ወቅታዊ የጥገና ዓይነቶች 359.41 ኪ.ሜ የነባር ገጠር መንገዶች ጥገና በማከናወን የ5 ወሩን ዕቅድ 121.75 % ፣የዓመቱን ዕቅድ ደግሞ 29.6% ማከናወን ችሏል፡፡ባለፉት 5 ወራት ከተከናወነዉ የጥገና ሥራ መካከል 308.41 ኪ.ሜ የሚሆነዉ በመሣሪያ እና በሰዉ ኃይል የጥገና ሥልት የተከናወነ መደበኛ ጥገና ሲሆን ቀሪዉ 51 ኪ.ሜ የሚሆነዉ ደግሞ ወቅታዊ ጥገና ነዉ፡፡
ጥገና ጽ/ቤቱ በአሁኑ ወቅት 102.43 ኪ.ሜ ርዝመት ባላቸዉ ከአጉለሽ- ቡሸት-ገደብ፣ከሰዴ-ከርነዋሪ፣ከአዲስቅዳም- ችጓሌ፣ከችጓሌ- ጥርጊ፣ከባካፍታ - መሰላ፣ከመሰላ - ዋይከላ እና አዲስቅዳም-ፋግታ 7/ሰባት/ የጥገና መስመሮች በመደበኛ እና በወቅታዊ የጥገና ዓይነቶች ጥገና እያከናወነ ሲሆን የጥገና ሥራዉን በወቅቱ ለማጠናቀቅ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት በምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም እና አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞኖች በሚገኙ ነባር የገጠር መንገዶች የጥገና ስራ የሚያከናዉን ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት በ68 የጥገና መስመሮች 1,213.22 ኪሜ የነባር ገጠር መንገዶች ጥገና በማከናዉን ህብረተሰቡ ተገቢዉን የመንገድ ትራንሰፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ እየሰራ ይገኛል፡፡



